ህወሃት ተላላኪ ሁኖ በርካታ በደሎችን በሕዝብ ላይ ሲፈጽም የነበረው ደረጀ መከታው የተባለው ግለሰብ በአርበኞች ግንቦት 7 የውስጥ አርበኞች እርምጃ የተወሰደበት መሆኑ ታወቀ

0

አባይ ሚዲያ ዜና
ብርሃኑ አየለ

ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት7  የውስጥ አርበኞች የተገደለው ደረጀ መከታው የተባለው ግለሰብ ከዚህ በፊት በቀድሞው የኢትዮጵያ  ሕዝብ አርበኞች  ግንባር አባል የነበረ እና በድርጅቱ  ግዳጅ በመላክ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ አብሮት ሲሄድ የነበረውን የትግሉን ጓዱን በመካድና የጠላት ተባባሪ በመሆን በታጠቀው የድርጅቱ መሳሪያ በመግደል ለወያኔ ስርአት እጁን በመስጠት ተቀላቅሏል። ከአገዛዙ ተቀላቅሎ በመኖር ላይ እያለም ከአንድ የስርአቱ አገልጋይ ጓደኛው ጋር በመሆን የትጥቅ ትግሉን ይደግፋሉ እንዲሁም በገዢው ቡድን ላይ ሕዝቡን ያሳምጻሉ ብለው የሚፈርጇቸውን ሰዎች እንዲሰልሉ በአገዛዙ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረ ቢሆንም ከእለታት አንድ ቀን ሰው በመግደል  ታስረው የቆዩ ሲሆን  ባልታወቀ ምክንያትም ብዙም ሳይቆዩ ከእስራት ተፈተዋል።

ይሄው ደረጀ መከታው የተባለው ግለሰብ  ከእስራት ከተለቀቀም በኋላ ከወያኔ ደህንነት ጋር በመሆን በአሳቻ ሰዓትና በማታ ንጹሀን ዜጎችን በማደን ሲአሳስርና ሲአስደበድብ በተጨማሪም ሲአስገድል ሲገድል መቆየቱን የአካባቢው ሕዝብ የዐይን ምስክሮች ናቸው። በመሆኑም ይህንን የሕዝብ ሰቆቃ ሰምቶ መታገስ ሂሊናቸው ያልፈቀደላቸው በአርበኞች ግንቦት7 ስም በአገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የውስጥ አርበኞች  በዚሁ ደረጀ መከታው በተባለው  ግለሰብ ሕዝብ  የሚደርሰበትን በደልና  ይህው ግለሰብ ለወያኔ መላላክን ምርጫው ያደረገ በንጹሀን ዜጋ ሞት የሚደሰት መሆኑን በመመልከታቸው የአርበኞች ግንቦት7 የውስጥ አርበኞች ተከታትለው ሊገድሉት ችለዋል።

አሁንም በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ከሕዝብ ጎን መቆም ሲገባቸው ለጥቅም ያደሩ ግለሰቦች መለስ ብለው መሳሳታቸውን አምነው ከሕዝብ ጎን ካልተሰለፉ እና የሕዝቡን ትግል ካልደገፉ ወይም ከቀደመው እኩይ ተግባራቸው ተቆጥበው ማሳሰራቸውን እና ማስደብደባቸውን እስካላቆሙ ድረስ በሰላም መኖር እንደማይችሉና የእነርሱም እጣ ፈንታ እንደ ደረጀ መከታው እንደሚሆን የአርበኞች ግንቦት7 የውስጥ አርበኞች ከአገር ቤት በአደረሱን መረጃ አስታውቀዋል።