የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዝን እንደዘገበው በባህርዳር ግራንድ ሆቴል የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ዜጎቹ ወደ ባህርዳር እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል። የኢምባሲው ሰራተኞች ወደ ባህርዳር እንዳይጓዙም እገዳ ጥሏል። ኢምባሲው በመግለጫው ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ የሚያስከትለውን አደጋ እየተከታተለ በማስታወቅ ላይ መሆኑን ጠቅሷል።

በባህርዳር የደረሰውን ፍንዳታ በተመለከተ ገዢው ፓርቲ የሰጠው መግለጫ የለም። ይሁን እንጅ በከተማዋ ፍተሻ በመካሄድ ላይ ሲሆን፣ በጥርጣሬ የተያዙ ወጣቶችና ድርጅቱ ሰራተኞቸ መኖራቸው ታውቋል።

ከፍንዳታው በፊት ሆቴሉ የሙዚቃ ዝግጅት ለማዘጋጀት መወሰኑን ተመልክቶ ፣ “በከተማው የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ ሙዚቃ ማዘጋጀት ትክክል አይደለም” የሚል  በፌስቡክ የተቃውሞ ቅስቀሳ ይካሄድ ነበር። በከተማው የሚገኙ ወጣቶች እንደሚሉት ሆቴሉ የብአዴን ከፍተኛ ሹሞች በእጃዙር የሚያስተዳድሩት ነው። የሙዚቃ ዝግጅቱ በክልሉ ሰላም ሰፍኗል የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር።