አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ

የአሜሪካ መንግስት በጎንደር ኢንታንሶል ሆቴል በደረሰው የቦምብ ጥቃት መሰረት በማድረግ ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያና እገዳ አውጥቷል።

በሆቴሉ በደረሰው ጥቃት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ወደ ስድስት መጎዳታቸውን የኢትዮጵያን ፌዴራል ፖሊስ ባቀረበው ሪፓርት መረዳቱን የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጻል።

በወያኔ ህውሃት በበላይነት በሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ የሚደረግ ጉዞ የሚያስከትለውን አደጋ ለአሜሪካ ዜጎች በየወቅቱ እንደሚገልጽም አሳውቋል።

ህዝቡ ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር በትጥቅ ትግል እየተፋለመባት ወደ ሚገኝው ጎንደር ከተማ የሚደረግ ጎዞንም የአሜሪካ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጌዜ ማገዱንም ገልጻል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በባህር ዳር ግራንድ ሆቴል የደረሰውን የቦምብ አደጋ ተከትሎ ኤምባሲው የአሜሪካ ዜጎች ወደ ባህር ዳር ጉዞ እንዳያደርጉ ማሳወቁም ይታወሳል።

በአማራ ክልል ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞች ከአገዛዙ ወታደሮች ጋር የሚያደርጉት የትጥቅ ፍልሚያ ቀጥሎ በርካታ የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውም ያታወቃል። ህዝቡን ማሰርና ማዋከቡም በመንግስት ሃይሎች በስፋት እንደቀጠለ በተለያዩ ጌዜ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ያለውን ውጥረት በመከታተል የአሜሪካ ኤምባሲ የጎዞ እገዳውን እያጠናከረ ይገኛል።

ሙሉውን መግለጫ ከታች በተቀመጠው ሊንክ ያገኙታል

 

Security Message for U.S. Citizens: Addis Ababa (Ethiopia), Explosion in Gondar