በጎንደር በትናንትናው ቀን በኢንታሶል ሆቴል የቦንብ ጥቃት ከደረሰ በኋላ በዛሬው ቀን ደግሞ የእሳት ቃጠሎ ተከስተ

0

አባይ ሚዲያ ዜና

በዛሬው ቀን የደረሰው የእሳት ቃጠሎው የደረሰው በልደታ ንዑስ የከተማ አስተዳደር ህንፃ ለመሆኑ እሳቱ ሲነድ የሚታየው ከዚያ መሆኑን በዐይኑ የተመለከተው የዜና ምንጫችን የእሳቱ መንስዔ ግን ምን እንደሆነ ማረጋገጥ አለመቻሉንም ጨምሮ ገልጿል።

ወያኔ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በኋላ ተፈጥሮ የነበረውን አለመረጋጋት ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሬ በአገሪቱ ሰላምን እና መረጋጋትን መልሻለሁ በማለት ተደጋጋሚ መግለጫ ሰጥቷል። ሕዝቡንና የውጭ ዜጎችን ለማረጋጋት ተደጋጋሚ መግለጫ ቢሰጥም በተግባር የሚታየው ግን የዚህ ተቃራኒ የሆነው የሰላም መደፍረስና ሊቆጣጠሩት ያልቻሉት ከመቅጽበት የሚለዋወጥ ሁኔታ ነው።

በውስጥም በውጭም የሚገኙ የሲቪሉ ሕብረተሰብ አባላት እና የፖለቲካ ታዛቢዎች መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አቁሞ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ቁጭ ብሎ በጽሞና በመነጋገር የሕዝቡን ጥያቄ በአስቸኳይ ካልፈታ አሁን ያለው ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ከቁጥጥር እንደሚወጣ እያስጠነቀቁ ነው።